ቴስላ አንድ ጊዜ በተሞላ የኤሌክትሪክ ሃይል ከ800 ኪሎ ሜትር በላይ የሚጓዝ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ይፋ አደረገ

ቴስላ የመኪና አምራች ኩባንያ አንድ ጊዜ በተሞላ የኤሌክትሪክ ሃይል ከ800 ኪሎ ሜትር በላይ የሚጓዝ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ይፋ አደረገ።

ቴስላ ሰሚ የተሰኘው ይህ ተሽከርካሪ በኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሎን መስክ ነው ይፋ የሆነው።

መስክ በካሊፎርኒያ እስከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ድረስም አሽከርከርታል።

ቢሊየነሩ ስራ ፈጣሪ ኤሎን መስክ ተሽከርካሪው ሙሉ ጭነት ይዞ በሰዓት ከ104 ኪሎ ሜትር በላይ በሰዓት እንደሚጓዝ ነው የገለፀው።

የትራንስፖርቱን ዘርፍ ለማዘመን ራዕይ ይዞ የተነሳው የሙስክ እቅድ፥ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ ያተኮረ ነው።

በዚህም በአሜሪካ ከሚለቀቀው በካይ ጋዝ ሩብ ያህሉን የሚሸፍነውን እና ከተሽከርካሪዎች የሚወጣውን በካይ ጋዝ ለመቀነስ በኤሌክትርክ ሃይል የሚንቀሳቀሱ መኪኖችን በማምረት ላይ ነው።

በፈረንጆቹ 2019 ግንቦት ወር የከባድ ጭነት ተሽከርካሪው ምርት በይፋ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

መስክ አዲስ የስፖርት ውድድር መኪና ሞዴልም ይፋ አድርጓል።

በአንድ ጊዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ሙሌትም እስከ 1 ሺህ ኪሎ ሜትር ኪሎ ሜትር ሊጓዝ ይችላል ተብሏል።

ይህ የስፖርት ተሽከርካሪ በሰዓት ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ በሰዓት ይጓዛል።

Comments

comments