ሞዚላ ፋየርፎክስ “ኳንትም 57” የተባለ ፈጣን የኢንተርኔት ብሮውዝር አቀረበ

ሰዎች ሞዚላ ፋይርፎክስ በሮውዘር (የኢንተርኔት መክፈቻ) መጠቀም አቁመው ፊታቸውን ወደ ጎግል ክሮም እንዲያዞሩ ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ፍጥነት ነው።

ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ሞዚላ በኢንተርኔቱ ዓለም የነበረውን ስፍራ ዳግም መልሶ ለመያዝ በሚል በፍጥነት ዙሪያ ሲሰራ ቆይቷል።

ሞዚላ ይህንን እውን ለማድረግም ኳንተም የሚል ፕሮጀክት በመቅረፅ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፥ ይህ ፕሮጀክትም የሞዚላ ፋየርፎክስን ፍጥነት በእጅጉ የቀየረ ነው።

ኩባንያው በዚህ ፕሮጀክትም “ፋየርፎክስ 57” የኢንተርኔት መክፈቻ (ብሮውዘር) የሰራ ሲሆን፥ ብሮውዘሩንም ባሳለፍነው መስከረም ወር ነበር ይፋ ያደረገው።

new_tab.png

አሁን ደግሞ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች “ኳንትም 57” የተባለውን ፈጣኑን የኢንተርኔት መክፈቻ ኮምፒውተራቸው ላይ አውርደው እንዲጠቀሙ አቅርቧል።

“ፋየርፎክስ 57” የኢንተርኔት መክፈቻ ዊንዶውስ፣ ሊኑክስ እና ማክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ኮምፒውተሮች ላይ የሚሰራ መሆኑም ተነግሯል።

አዲሱ የፋየርፎክስ 57 ብሮውዘር ፍጥነት በእጥፍ የጨመረ ሲሆን፥ ከጎግል ክሮም ጋር ሲነፃፀርም የሚጠቀመው ራም መጠን በ30 በመቶ የቀነሰ ነው።

የኢንተርኔት መክፈቻ (ብሮውዘሩን) በዚህ ያገኛሉ፦ The new Firefox

Comments

comments