ሆማ ኮንስትራክሽን የከፍተኛ ማዕድን ማምረት ፈቃድ ተሰጠው

የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ለሀገር በቀሉ ሆማ ኮንስትራክሽን የከፍተኛ ደረጃ የላይምስቶን እና ጂፕሰም ማዕድን ማምረት ፈቃድ ሰጠ፡፡

ስምምነቱን የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ እና የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዱኛ እጅጉ ናቸው የተፈራረሙት።

የውል ስምምነቱ ለ20 ዓመታት የሚፀና ሲሆን፥ ስምምነቱ ሲጠናቀቅ ከ10 ዓመታት ላልበለጠ ጊዜ ሊታደስ እንደሚችል በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ባጫ ፋጂ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

motuma2.jpg

ሆማ ኮንስትራክሽን ፈቃድ ያገኘው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ ኢሉ-ዴኩ፣ ኢሉ-ጎሎሌ እና ዴኩ-ከሬሳ በተባሉ አካባቢዎች ሲሆን የቆዳ ስፋቱም 13 ነጥብ 4587 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው ብለዋል።

ኩባንያው ለኢንቨስትመንት ወጪ ከ98 ሚሊየን 891 ሺህ ብር በላይ መመደቡን ነው አቶ ባጫ የጠቆሙት።

በዓመት በአማካይ 1 ሚሊየን ቶን የላይምስቶን እና ጂፕሰም ማዕድን ያመርታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

ኩባንያው ለኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ቅድሚያ የስራ ዕድል የመፍጠርና ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ሥልጠናዎችን የመስጠት ግዴታ ተጥሎበታል።

Comments

comments