የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ የሚካሄድበት ጊዜ በ9 ቀናት ተራዘመ

የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን በድጋሚ የሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፈረንጆቹ ጥቅምት 26 ቀን እንዲካሄድ ወሰነ።

የድጋሚ ምርጫው የሚካሄድበት ጊዜ በዘጠኝ ቀን የተራዘመው ኮሚሽኑ የመርጫ ሂደት ማሻሻያዎችን ለማድረግ ጊዜ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ ነው።

ኮሚሽኑ በምርጫው ሁለቱ ዋነኛ ተፎካካሪዎች ብቻ እንደሚሳተፉም ይፋ አድርጓል።

በፈረንጆቹ ጥቅምት ወር በሚደረገው ምርጫ፥ የወቅቱ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታና ተፎካካሪያቸው ራይላ ኦዲንጋ ብቻ ይሳተፋሉ ነው ያለው ኮሚሽኑ።

ከአንድ ወር በፊት በተካሄደው ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ አብላጫ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ገልጾ ነበር።

ይሁን እንጅ የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምርጫው ከተካሄደ ከጥቂት ቀናት በኋላ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል የቀረበለትን አቤቱታ በመቀበል የምርጫውን ውጤት ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

የምርጫ ኮሚሽኑን የተሳታፊዎች ዝርዝር ተከትሎ ግን ሌሎች ተፎካካሪዎች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንወስደዋለን ብለው ነበር።

በምርጫው በሰፊ ልዩነት የተሸነፉ ተፎካካሪዎች በድጋሚ ምርጫው ሌሎች ተፎካካሪዎችም ስላለን ልንካተት ይገባል ብለዋል።

Comments

comments