ይድረስ ለቤተ አማራ ፣ልሣነ አማራ ፣ምስጋናው አንዷዓለም ፣አያሌው መንበሩ፣ለፋርጣ እድርተኞችና ጎንደር ህብረት ። ከቅማንት ዱሁጋ የተላከ። 

ትምክህተኝነት ዘረኛና ፀረ-ብሄረ ብሔረሰብ ሲሆን መገለጫውም በቅማንት ላይ የሚያደርገው ተንኮል ነው።

 

ዘረኝነት ማለት የራስክን ዘር ወይም ቡድን ከፍ ከፍ እያደረክ የሌሎችን የምታሳንስበት አስተሳሰብና አሠራር ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመሠረታዊ እውነታ ላይ የተመሠረታ ሳይሆን የግል ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ዘረኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጸንሶ የሚወለደው ውስጣቸው ሠይጣን በሸመቀባቸው ግለሠቦች ሲሆን ቀስ በቀስ የግለሰቡ የዘረኝነት በሽታ በሚኖርበት ቡድን ውስጥ ይገባል፡፡ በዚህም ዘረኝነት የቡድኑ በሽታ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ዘረኝነት የቡድን በሽታ ሆነ ማለት በቡድኑ ውስጥ ያሉ ሁሉ ሰዎች ዘረኞች ሆኑ ማለት አይደለም፡፡ አብዛኛው ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ዘረኝነት ብዙውን ጊዜ የሚመነጨው ወይም የሚወለደው ከቡድኑ ወይም ማህበረሰቡ ልሂቃን ስለሚሆንና እነዚህ ልሂቃንም በማህበረሰቡ የሥልጣን ተዋረድ ላይ ተጽእኖ ስለሚያሳድሩ ቡድኑ ዘረኝነትን ባይቀበለውም ተሸክሞት ይጓዛል፡፡ መቼም አህያ የምትጫነውን ነገር ወዳ በነጻ ፍላጎቷ አትጫንም፡፡ እንደዚሁ ሙሉ ዘረኝነትን የማህበረሰቡ ልሂቃን ወልደው፣ አሳድገው፣ ከሌላው የማህበረሰቡ አባላት ጋር በሃይልም ሆነ በጥቅማጥቅም ደልለው ያጋቡታል፡፡

 

ዘረኝንት በማህበረሰቡ ዘንድ ጸንቶ የእለት ከእለት ንግግራችንና ሥራዎቻችን አንዱ ክፍል ሆኖ እንዲቀጥል እነዚህ ልሂቃል የሚችሉትን ሁሉን የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅመው ያራግባሉ፡፡ ስለራሳቸው ጥሩነት ይሰብካሉ፡፡ ይሄ ባልከፋ፤ የሌሎች ቡድኖች እሴቶች፣ የማንነት መገለጫዎች፣ አስተሳሰቦችና አሠራሮች ትክክል እንዳልሆኑ ያራግባሉ፡፡ ለሌሎች ቡድኖችና ህዝቦች ልዩ ልዩ የማዋረጃና ማንቋሸሻ ስያሜዎችን ያወጡና ይለጥፉባቸዋል፡፡ ይህንንም በራሳቸው ማህበረሰብ ዘንድ እንዲያድግና ሰዎቻቸው በእለት ከእለት መስተጋብሮቻቸው ውስጥ እንዲተገብሯቸው ያደርጋሉ፡፡ ምንም ይሁን ምን እነሱ የጠሉት ቡድን መልካም ነገር ቢሠሩ ከምንቋሸሽ አይመለሱም፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡- ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ድንቅ ድንቅ የአምላክነት ሥራዎችን እየሠራ የአይሁድ ሊቃነ ክህናትና ካህናት (ልሂቃን) እንዳይቀበሉትና አምነው እንዳይድኑ ያደረጋቸው አንዱ ትልቁ ነገር ሠይጣን በልባቸው ያሳደረባቸው የዘረኝነት በሽታ ነበር፡፡ “መሲህ ከገሊላ ለዛም ከድሃ ቤተስብ አይወለድም” እያሉ ተዘባበቱበት፡፡ የሚሰራቸውን ድንቅ ተአምራት እያዩ አይናቸውን ጨፍነው ካዱት፡፡ በሦስተኛው ቀን መነሳቱን አይተው ከማመን ይልቅ መቃብር ሲጠብቁ ለነበሩት ወታደሮች መማለጃ ወርቅ ሠጥተው እየዞሩ በየከተማው “እኛ ተኝነትን ሳለ ደቀመዛሙርቱ መጥተው ሰርቀው ወሰዱት እንጂ አልተነሳም” እያሉ እንዲመሰክሩ በማድረግ ራሳቸው ጠፍተው ብዙዎችን አጠፏቸው፡፡ በቃ! አንድ ሰው ወይም ቡድን ዘረኛ ከሆን የሚሠራው ይሄ ነው፡፡

 

ዘረኛው ቡድን የሚፈልገውን በፕሮፓጋንዳውና በጥቅማጥቅሙ ማሳካት ካልቻለ ወደ አሸባሪነት ይረማመዳል፡፡ እኔ ምልህን ካላደረክ እገድልሃለሁ፡፡ እያሉ ያስፈራራሉ፤ ሲመቸውም ይገድላል፤ ያዋክባል፤ ወዘተ፡፡ ልክ ቅማንቱ ላይ ሲደረግ እንደቆየውና አሁን እየተደረገ እንዳው ማለት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ዘረኝነትና ትምክህተኝነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ትምክህትኝነት ማለት ዘረኝነት ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የራሱን ቡድን እየካበ ሌሎችን ማዋረድ፤ የራሱን አዋቂነት እየነገረን የሌሎችን ድንቁርና መስበክ፤ የራሱን ሶሎሞናዊነት እያወጀ የሌሎችን ዲቃላነት ማውራት ልማዱ ስለሆን ነው፡፡ “እኔ ነኝ ትክክል እናንተ ትክክል አይደላችሁም” ማለት ትምክህተኝነት ሲሆን መሠረታዊ ምንጩ ዘረኝነት ነው፡፡ አዎ ትምክህተኝነት ዘረኝነት እንዳይመስል የሚያራግበት መንገድ ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ “እናንተ የብሔር ብሔረሰብ መብቶች የተከበሩበት ኢትዮጵያዊነት የምትሉት ነገር ዘረኝነትን ማስፋፋት ነው” እያሉ ያራግባሉ፡፡ በትምክህተኝነት እሳቤ ኢትዮጵያዊነት ማለት ብሔር ብሔረሰብ የሚባል ሳይኖርና ራስን በራስ ማስተዳደር የሚባል አስተሳሰብና አሰራት ሳይኖር ዝም ብሎ ሾላ በድፍኑ ኢትዮጵያዊ መሆን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የእነሱ አስተሳሰብና አመለካከት እንዲሁም አሠራር እንጂ የሌለች አይደለም፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች ማንነታቸው ተከብሮላቸውና ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ኢትዮጵያዊነታቸውን በእኩልነት ላይ መስርተው እንዲያጣጥሙት ያደረገላቸውን የኢፌዲሪ ሕገመንግስት የተቀበሉ ቢሆንም ጥቂት የትምክህተኝነት ዘረኝነት ሠይጣን የተሳፈረባቸው ግለሠቦችና ቡድኖች ከዚህ በአንጻሩ ተሠልፈው ይህን ሕገመንግስት በማጥፈት የህዝቦችን ማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር እስከ መገንጠል መብት ድምጥማጡን ለማጥፋት ይኳትናሉ፡፡

 

አንድነት እኔ ቅማነት ነኝ፣ እኔ አማራ፣ እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ እኔ ትግራይ ነኝ፣ እኔ አርጎባ ነኝ፤ ወዘተ ሳይባል መሆን አለበት ይሉናል፡፡ አስተዳደርም መከለል ያለበት መልክዓ ምድር ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት እንጂ ብሔርን መሠረት አድርጎ መሆን የለበትም ይሉናል፡፡ ለእኔ ይህ ኢትዮጵያዊነት የብሄር ብሔረሰብ ማንነትን ማፈኛ ዝተት ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ሞክረነዋል፡፡ በሃገሪቱ የአንድ ቡድን አስተሳሰብና አሠራር የበላይነት ይዞ ሌሎች በማንነታቸው እንዲሸማቀቁ ያደረገ አንድነት ነበር፡፡ እኔ በራሴ ቋንቋ እንዳልተዳደር ተደርጌ የገዢ መደቡን ቋንቋ በግድ እንድናገር ተጫነብኝ፤ ይህን የገዢውን ቋንቋ አሳምሬ መናገር ባለመቻሌ ደግሞ “ገመድ አፍ፤ ተብታባ፣ ወዘተ” ተባልኩ፡፡ ቅማንቱም ሲደረግበት የነበረው እንደዚህ ነው፡፡ “አጥምቀነሃልና አማራ ነኝ በል” ተብሎ የማይፈልገውን ማንነት ጫኑበት፡፡ የሚገርመው ቅማንቱ “አማራ ነኝ” ብሎ እንደ አማራው መሆን ሲፈልግ ደግሞ “አንተ ቆራጣ ቅማንት፣ አንተ እንጨት አምላኪ፣ አንተ እሬት፣ አንተ የሰሳ ልጅ፣ አንተ ጅራታም፣ ወዘተ” እያሉ ሲሰድቡን እና ሲያሰድቡን ኖሩ፡፡ በቆይታ፣ መቼም ጊዜ መልካም ነው፤ የብሔርና ብሔረሰቦችን ጭቆና አሸቀንጥሮ የጣለ ሕገመንግስት መጥቶልን መብታችን ተጠቅመን “አዎ ቅማንቶች ነና ማንነታችን ተከብሮልን ራሳችን በራሳችን እናስተዳድር” ብለን ጥያቄ ስናቀርብ “የለም እናንተማ አማራዎች ናችሁ፤ ተጠምቃችኋል፤ ተጋብተናችኋል፤ ቋንቋችሁ ጠፍቷል፤ ባህላችሁ ሙቷል፤ በህላችሁንና ቋነቋችሁን እኛ ራሳችን አሳድገን ስናበቃ ማንነታችሁን እናከብርላችኋለን” እያሉ አሾፉብን፡፡ ጥያቄያችን እየተጠናከረ በመሄዱ እና ሕገመንግሥታችንም ከእኛ ጎን ቆሞ ቅማንትነታችን እውን ሲሆን ደግሞ ጦር ጎመድ የያዙ ህገወጦችን አሰባስበው ገደሉን፣ አሳደዱን፣ አሰሩን፣ አፈናቀሉን፣ ቤቶቻችንና ንብረቶቻችን በእሳት አጋዩብን፣ ብዙውን ንብረታችን ደግሞ ዘርፈው ወሰዱብን፡፡

 

ይህንም ተቋቁመን ትግላችን በመቀጠላችንና አስተዳደራችን ወደ መመስረቱ ዋዜማ ስንደርስ አይን ያወጣ ዘረኝነታቸውን ማቀርሸት ጀምረዋል፡፡ ህዝበ ውሳኔ የሚሠጥባቸው 12 ቀበሌዎች ተለይተው ወደ ሥራ ሲገባ በኪራይ ሰብሳቢነት በኩል የተሰለፈው ትምክህት ምርጫውን ለማደናቀፍ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ የተወሰኑ ቀበሌዎች የሚኖሩ ቡችሎቻቸው ህዝቡን እንዲያምሱ አድርገው የምርጫ ምዝገባው እንዲጓት እያደረጉ ነው፡፡ ምዝገባ በተጀመረባቸው ቀበሌዎች ደግሞ የማይመለከተው ማለትም የምርጫው ህግ የማይፈቅድለትን ሰው እየጎተቱ በግድ ያዝመዘግባሉ፡፡ የጸጥታ ሃይሉ የምዝገባ ጣቢያዎች ውስጥ ገብቶ ይፈተፍታል፤ ኪራይ ሰብሳቢ አመራሩ ራሱ ታዛቢ ይሆናል፤ የምርጫ ጣቢያን በፈለገው ቦታ ይወስዳል፡፡ የቅማንት ታዛቢዎችን ሌሊት ሌሊት እየዞሩ ያስፈራራሉ፡፡ ወሮበላ አዘጋጅተው ሊመዘገም የሚመጣ ቅማንት እንዲሸማቀቅ የማያደርጉት የለም፡፡ ስድብና ማዋረዱንማ ተውት፡፡ በፌስ ቡክ ጫካ የሸፈቱት ትምክህተኞች ደግሞ ቅማንት የሚባል የተማረ ሰው ወይም በቅማንት እንቅስቃሴ ውስጥ በኮሚቴነት የሚያገለግሉ ግለሠቦችን ስም ማጥፋት፣ ማስፈራራት፣ ፎቷቸውን መለጠፍ፣ ወዘተን አጧጡፈው ቀጥለዋል፡፡ ከፌስ ቡክ ማዘዣ ጣቢያቸው ተወሽቀው እከሌን ግደል፣ እከሌን አፍን፣ እከሌን ቆርጭማቸው፣ ወዘተ እያሉ ያዋጋሉ፡፡ ደግነቱ የሰማቸው ወይም የሚሰማቸው የለም፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ወከባና መንፈራገጥ ምን አመጣው ብለን ስንጠይቅ መልሱ ዘረኝነት የወለደው ትምክህተኝነት ነው፡፡ “እኔ የምሠጥህን ብቻ ውሰድ፤ አንተ ዴሞክራሲያዊ መብትህን መጠቀም አትችልም፤ ወዘተ” እያሉን እንደድሮው አባቶቻቸው ዛሬም አፍነው ሊገዙን ታጥቀው ተነስተዋል፡፡ ዛሬም እነሱ አንድነት፣ ሃይማኖት በሚሉት የማንነት ማፈኛ ኮተት ሊጠቀልሉን ይፈልጋሉ፡፡

 

የቅማንትን ቅማንትነት የሚወስነው ሕገ መንግሥታችን በሚፈቅደው መሠረት ራሱ የቅማንት ህዝብ እንጂ ሌላው ህዝብ ሊሆን አይችልም፡፡ አሁን ዘመነ ዴሞክራሲ እንጂ ዘመነ መሳፍንት ወይም ዘመነ ዘውድ እንዳልሆነ ማወቅም ሆነ ማሰብ በጭራሽ አይፈልጉም፡፡ ብቻ ተጨፍነው ወንጀል ይሰራሉ፡፡ ይዋሻሉ፡፡ እንዴ! ዛሬ በዚህ ዘመን ዴሞክራሲን ያልተቀበሉ እነዚህ ሰዎች መቼ ነው የሚበስሉት? ይገርማል! አንዳንዴ ሳስበው ይህቺ በስሟ ሲነገድባት የኖረች ምስኪኗ ኢትዮጵያ ስንቱን ደንቆሮ ነው ተሸክማው የመጣችሁ እላለሁ፡፡ አሁንም ከዚህ ድንቁርናቸው ጋር በማይፋታ የቃል ኪዳን ጋብቻ የተገቡት ቁጥራቸው የትየለሌ ነው፡፡ ምንም ትምህርት አይገባቸውም፡፡ እንዲያውም ሲማሩ ይደነቁራሉ፡፡ አሁን ፌስቡክ ላይ ዝም ብለው በሜዳ የሰውን ስም የሚያጠፉትና በቅማንት ላይ ጦርነት የሚያውጁት እኮ ፊደል ቆጠርን የሚሉ ግለሰቦችን የሰበሰበ የደናቁርት ህብረት ወይም ማህበር ነው፡፡ በቃ የሚያላዝኑት ስለራሳቸው ማንነት ማደግና አለማደግ ሳይሆን “የሎሎች ማንነት ለምን ይፈቀዳል?” በሚል ሠይጣናው ምቀኝነት ላይ ተመስርተው ነው፡፡ ይገርማ! አማራው የራሱን ብሄራዊ መብት በደንብ በመጠቀም ልማትና ብልጽግና እንዴት አድርጎ ማምጣት እንዳለበት ከመሥበክ ይልቅ ሌሎች ብሔር ብሔረሰብ ለምን ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድራሉ በሚል የቅናት ዛር ይንዘረዘራሉ፡፡ በእርግጥ ይህ የሰፊው የአማራ ህዝብ ጥያቄ አይደለም፡፡ ነገር ግን አስተሳሰባቸውን በአማራው ህዝብ ላይ በመጫን ቅማንትን ለማስጨፍጨፍ ይውተረተራሉ፡፡ ከውጭ እስከ ውስጥ ያሉ የተንኮል ድር አባሎቻቸው ይህን ለማድረግ ተግተው እየተንደፋደፉ ነው፡፡

 

ለማንኛውም ወደ ተነሳሁበት ርእስ ልመለስና ይህ እስካሁን ከላይ ያቀረብኩት ሁሉ የትምክህት ልብራሱ ዘረኝነት ነው፡፡ ዘረኝነት ማለት በዘር ላይ የተመሰረተ ተግባርና እሳቤ ብቻ አይደለም፡፡ ዘረኝነት በቡድንተኝነት ውስጥ አለ፡፡ አንድ ቡድን የኔ ብሎ ካሰብ ከቡድኑ ውጭ የሆኑ ሰዎችንና ቡድኖችን የሚጠላ ከሆን ዘረኛ ነው፡፡ አዎ ከላይ ለመጥቀስ በሞከርኩት የዘረኝነት ትርጉም መሠረት ይህም ዘረኝነት ነው፡፡ ትምክህት በፍጹም የሌሎችን ነጻነት አይፈልግም፡፡ ማንኛውም ህዝብ በእነሱው አስተሳሰብ እንዲኖር ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የሚሉ ጽንሰ ሃሳቦች በአእምሯቸው ውስጥ እድል ፈንታ ጽዋ ተርታ የላቸውም፡፡ እነዚህ ነገሮች ለትምክህተኞች አለርጂዎች ናቸው፡፡ የብሄር ብሄረሰብ መብት ይከበር የሚል ቃል ሲሰሙ ይነስራቸዋል፤ ዓይናቸው ደም ይለብሳል፤ ለመናገር ምላሳቸው የቆለፋል፤ ጆሮዋቸው ይደነቁራል፡፡ በጣም የሚገርመው ደግሞ ይህን እሳቤያቸውን በአደባባይህ ህዝብ በተሰበሰበው መድረክ አይናገሩም፡፡ ከተናገሩም አስመስለው በለቁማጣ ምላሳቸው ደልለው ያልፋሉ፡፡ ከመድረክ በስተጀርባ ግን ጦር ይሠብቃሉ፡፡ በቃ በአሁኑ ዘመን ያለው የትምክህተኞች ሥራ ይህ ነው፡፡ በመድረክ ላይ “የቅማንትን መብት ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ እንመልሳለን እናስመልሳለን” እያሉ ሲያወሩ ይውሉና ለኢሳት ተቃራኒውን ማለትም እውነተኛ ፍላጎታቸውን ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ አስታውሳለሁ ከማውራው ጭፍጨፋ ማግስት ትምክህት ወደ 600 የሚሆኑ የአማራና ቅማንት ተወካዮችን ጠርቶ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ አምባ መሰብሰቢያ አዳራሺ ሰብስቦ “ለተፈጠረው ችግር ይቀርታ ጠይቀናል፡፡ ያዘመትነው ወታደር የሰራው ሥራ ህገወጥ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት ችግር አይፈጠርም” በማለት ሲልመጠበጥ ውሉ ከስብሰባው ማግስት በእነ መቶ አለቃ ደጀኔ ዘፋርጣ ወአጋንንት የሚመራ የወሮበላ ቡድን በማደራጀት የመተማንና የጭልጋን ቅማንቶች አስጨፈጨፉ፡፡

 

በቃ ትምክህት እንዲህ ነው፡፡ የቅማንት ህዝብ ሆይ ንቃ! ለትምክህት ልብህን እንዳትሰጥ፡፡ በፍጹም ትምክህት አፈጣጠሩ ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦችን ለማጥፋትና የራሱክ ከርስ ለመሙላት፤ ለመብላትና ለማራት ብቻ ስለሆነ ሎጂክ ይገባዋል ብለህ መጃጃል አይኖርብህም፡፡ ትምክህት ጥፋት ነው፡፡ ትምክህት ውንብድና ነው፡፡ ትምክህት ሌባ ነው፡፡ ትምክህት ፋርጥኛነትና ቀማኛነት እንጂ ዴሞክራሲያዊ አይደለም፡፡ ትምክህት ጠፍቶ አጥፊ ነው፡፡ ለዚህ ቡድን እጅህን እንዳትሰጥ፡፡ እንዳመጣጡ መልስ መስጠት ነው፡፡ እንጂ ሰብሶት የመጣውን የተንኮል ካባ አይተህ አትፍራው፡፡ መቼም እያዋረደህና እየሰደበህ የሚመጣ ህጋዊ ሰው የለም፡፡ እየሰደበህና እያዋረደህ እንዲሁም እያሸማቀቀህ አክብረኝ ቢልህ ዝም እንዳትለው፡፡ እንደሚገባው መልስልት፡፡ ትምክህት ሲፈሩት አይወድም፡፡ ከፈራኸው በቃ አለቀልህ፡፡ እስካሁን እንደታገልከው ሁሉ አሁንም ገና ብዙ መራራ ትግል ይጠብቅሃል፡፡ ትምክህት አሁን እንደገና አቆጥቁጧል፡፡ አይደለም ለቅማንት ህዝብ በአሁኑ ሰዓት ለኢትዮጵያ መላው ህዝቦች ሥጋት ነው፡፡ እናም በምርጫው ማጭበርበሩ እንደማይቀር ከወዲሁ እየተደረገ ያለውን ነገር ተመልክተሕ ምርጫህን በጥንቃቄ አድርግ፡፡ ተመካከር፡፡ ቀድመህ የትምክህቱን ሴራ አክሽፍ፡፡ ትምክህትን አትፍራው መፍራት ያለብህ ሕገመንግሥቱን ብቻ ነው፡፡ ትምክህት ሕገወጥ ነው፡፡ አንተ ሕጋዊ ነህ፡፡

 

ይህን ሕገወጥ ቡድን ከፈራኸው ከጆሮህ ላይ ይሸናብሃል፡፡ በደምህ እያስከበርከው ያለውን ማንነትህን አሳልፈህ እንዳትሠጥ፡፡ ይህ ጉዳይ ደግሞ ምርጫ በሚከናወንባቸው ቀበሌዎች ብቻ ጉዳይ አይከለም፡፡ ትምክህት ልዩ ልዩ ምክንያት እየፈጠረ የመተማን ቅማንት ቆርጦ ማስቀረት ይፈልጋል፡፡ ከዛም ሽንፋን እገድባለው በሚል የመተማን ቅማንት በታትኖ በማስቀመጥ ቅማንትን ከመተማ መንቀል ይፈልጋል፡፡ ይህን ህልሙን ለማሳካት ደግሞ አሁም በነጋዴ ባህር ምርጫ “ለ” ላይ እያደረገው ያለው ውንብድናና ሥርዓት አልበንነት ማሳያ ነው፡፡ ድሮውንም ትምክህት ቅማንትን ከነጋዴ መባህር በታች አናስወርደውም ሲል የቆየ ስለሆነና ህልሙን ለመፈጸምም ተግቶ ስለሚሰራ ይህ ዘረኛ ትምክህት ዝም ብለህ እንዳታይ፡፡ በያለህበት በንቃት ምርጫውን በመከታተል ህግንና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ እንደእስካሁኑ ትምክህትን እያዋረድክ መብትህን እያስከበርክ መሄድ ግድ ይልሃል፡፡ የትምክህተኞች ትልቁ ተንኮል በቅማንት ህዝብ እያንዳንዷ እርምጃ መካከል እንደ ፈንጂ የተጠመደ ነው፡፡ አንዱን ስታሸንፈው ሌላውን የተኩብሃል፡፡ አሁን በምርጫ ምዝገባው እያጭበረበሩ ነው፡፡ ነገ ደግሞ የምርጫው እለት ለማጭበርበር ሰው መድበው እየሰሩ ነው፡፡ ያንንም በድል አልፈሕ ወደ አስተዳደር ምስረታው ስትገባ ሌላ ወጥመድ ያጠምዳሉ፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ ትምክህት ታሪክ ሆኖ እስኪቀበር ድረስ መብትህን ማስከበር ግድ ይላል፡፡

ድል ለቅማንት ህዝብ ፤ ሞት ለጠባብ ትምክህተኞች !!

Comments

comments