በትንሽ ድንጋይ እስክትመታ አትጠብቅ!!

የኮንስትራክሽን ተቆጣጣሪው ከ 6ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ
የሚስራውን ሰራተኛ ይጠራዋል፣ ስራተኛው ሊስማው
አልቻለም፡፡

ስራተኛው የአሰሪውን ጥሪ ሊስማው ስላልቻለ ተቆጣጣሪው
መላ ዘየደ፡፡ እናም የሰራትኛውን ሃሳብ ልማግገኘት ሲል
ተቆጣጣሪው ከላይ ብር ጣለለት ብሩም ከሰራተኛው እግር ስር አረፈ፣ ሰራተኛው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አሰገብቶ ስራውን
ቀጠለ……

በድጋሜ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት ተቆጣጣሪው
መጀመሪያ ከጣለው ብር በላይ ሌላ ብር ጨምሮ ጣለለት፣
የቀን ሰራተኛውም ልከ እንደ መጀመሪያው ብሩን አንስቶ ወደ
ኪሱ አስገብቶ ስራውን ቀጠለ፡፡

በመጨረሻ ሌላ መላ ዘየደ ብር በመጣል የሰራተኛውን ሀሳብ
ማግኘት ስላልቻለ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት አነስ ያለ
ድንጋይ አነሳና ወደ ሰራተኛው ወረወረው፣ ድንጋዩም
የሰራተኛውን ጭንቅላት አገኝው በዚህ ሰዓት ነበር ሰራተኛው
ወደ ላይ የተመለከተው እና ከተቆጣጣሪው ጋር መነጋግር
የጀመረው፡፡
:
:
ይሄ ታሪክ ከእኛ ህይወት ጋር ይመሳሰላል ፈጣሪ ከኛ ጋር
መገናኘት ይፈልጋል ነገር ግን እኛ በጣም በ አለማዊ ስራ
ራሳችንን ጠምደናል ከዛ ፈጣሪ ትንሽ ስጦታ ይሰጠናል እኛም
ስራችንን እንቀጥላለን ከየት እንዳገኘነው ቀጥ ብለን ለማየት
ጊዜ የለንም፡፡

በድጋሜ ፈጣሪ ከመጀመሪያው የተሸለ ስጦታን ይሰጠናል
አሁንም ልክ እንደ መጀመሪያው ስጦታውን ወስደን
ምስጋናም ለፈጣሪ ሳናቀርብ እድልኞች ነን ብቻ ብለን
ስራችንን እንቀጥላልን ከየት እና ከማን እንዳገኘነው ቀና
ብለን ለማየት አንሞክርም፡፡

እናም በትንሽ ድንጋይ ስንመታ፣ ማለት ትንሽ ችግር ቢጤ
ስታገኘን ወደ ላይ ማየት እና መጮህ ከዚያም ከፈጣሪ ጋር
መነጋገር እንጀምራለን፡፡ ስለዚህ ምንግዜም በህይወታችን
ስጦታን ስናገኝ በፍጥነት ፈጣሪን ማመስገን አለብን በጭራሽ
በትንሽ ድንጋይ እስክንመታ መጠበቅ የለብንም ሁሌም ቢሆን
ከፈጣሪ ጋር እንገናኝ፡፡

Comments

comments