ጠቅላይ ሚንስትር መለስ  ዜናዊ  ማናቸው? by ልፋዓተይ ተስፋ

=======================

ጠቅላይ ሚንስትር መለሰ ዜናዊ (የትውልድ ስማቸው ለገሠ ዜናዊ አስረስ) (ሚያዝያ 30 ቀን 1947 ዓ/ም – ነሐሴ 14 ቀን 2004ዓ/ም) ተኣምረኛ እና እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ የነበሩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰው ናቸው። በዓድዋ ትግራይ የተወለዱ ሲሆን ከ1987ዓ/ም አንስተው እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን በከፍተኛው የአመራር ብቃት የምንስትሮች ጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታ ላይ ነበሩ። የኢህኣዴግና የሕውሓት ሊቀመንበር በመሆን ኢህኣዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ቆይተዋል።

 

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አባታቸው (አቶ ዜናዊ አስረስ) የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ  በእናታቸው በኩል ደግሞ ኤርትራዊ (ዓዲዃላ) ትግራወይቲ ናቸው።

 

ፊንፊኔ ከሚገኘው ጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ  በጊዜው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የኒቨርሲቲ በሚባለውና  የኣሁኑ ኣዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የህክምና ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ሳለ ትምህርታቸውን በማቋረጥ ህወሃት (የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባርን) ተቀላቅሉ፡፡

 

በጊዜውም የትግራይ ማርክሲስዝም ሌኒንዝም  ሊግን መሥርተዋል፡፡ ለገሥ ዜናዊ ሲወለዱ የወጣላቸው መጠሪያ ስማቸው ቢሆንም ቀስ በቀስ ግን በደርግ ሥርዓት በተሰዋው የትግል ጓዳቸው ስም መለስ ዜናዊ ተብለው ሊጠሩ ችለዋል፡፡

 

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ  ከኣጼ ኃይለስላሴ የኮከብ ተማሪዎች መካከል በእጅግ ከፍተኛ መዓረግ ሽልማት ከንጉሱ በግራ እጃቸው ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

 

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የሚመሩት ህወሓት የኮሎኔል መንግስቱ ኅይለማርያምን አምባገነናዊ መንግስት በትጥቅ ትግል ሲታገሉ ከነበሩ ድርጅቶች አንዱ ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ የህወሓት አመራር ኮሚቴ መሪ ሆነው በ1971 ዓ/ም ተመረጡ ፤ ቀጥሎም በ1979 ዓ/ም የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኑ። የደርግ መንግሥት ከወደቀም ጀምሮ የህወሓትና የኢህአዴግ ሊቀ-መንበርም ሆነው ኣገልግለዋል።  ኢህአዴግ የአራቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞከራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) ፤ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብኣዴን) ፤ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት ) ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ውህደት ነው። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ወደ ስልጣን ሲመጡ በጊዜው ለተቋቋመው የኢፌድሪ ጊዜያዊ መንግስት ፕረዚዳንት ሆነው ካገለገሉ በኋላ 1985 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ። በሃገሪቱ ኢትዮጵያን በበላይነት (በቁንጮነት) የሚመራ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚንስትር ፡ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ብቻ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በመፈንቅለ መንግስት ሳይሆን በጀግንነት በረሃ ወርዶ በጀብዱ እና የሰማይ ጠርዝ በደረሰ የዓውደ ውጊያ ጀግንነት ጠላትን ፡ ያውም ደርግን የመሰለ ሰው በላ ጭራቅን ፊት ለፊት በመፋለም ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብን ነፃ ኣውጥቶ እንደ ኩሩ ኣንበሳ እና እንደ ቁጡ ነብር ቤተ መንግስት ለመግባት የቻለ የምሁር ኮከብና የበረሃ ዘንዶ ታጋይነበር።

 

ትምህርትና ግላዊ ህይወታቸው ፦

================

 

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኘው ኦፕን ዩኒቨርሲቲ በ1988 ዓ/ም በማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስትሬት ዲግሪ ሲያገኙ ፤  በ1997 ዓ/ም. ደግሞ ኔዘርላንድ ከሚገኘው ኢራስመዝ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የማስተርስ ሳይንስ ዲግሪያቸውንና በጁላይ 1995 ዓ/ም. ደግሞ ደቡብ ኮርያ ከሚገኘው ሃናም ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል፡፡

 

የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ኣበርክቶዎች፦

========================

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከምንም ነገር በላይ አገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚወዱ ለዚች አገርና ሕዝብ የላቀ ራእይ የነበራቸው ቁርጠኛና ሃገራቸውን ወዳድ መሪ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ራእያቸውን እውን ማድረግ የጀመረና አስተማማኝ ውጤት ማምጣት የቻለ ድርጅትና መንግሥት የገነቡ ፤ ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ከፍ ብላ መጠራት እንድትጀምር ያደረጉ ታላቅና እጅግ አርቆ አሳቢ መሪ ነበሩ።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አገራችን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አቅጣጫ እንድትጓዝ ጥራት ያላቸው ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች ነድፈው በብቁ አመራራቸው በገነቧቸው ድርጅትና መንግሥት አማካኝነት ተግባራዊ ማድረግ የቻሉና በኣገራችን በመካሄድ ላይ ያለው ታላቅ አገራዊ የህዳሴ ጉዞ በሰመረ አቅጣጫ እንዲጓዝ ያደረጉ ታላቅ መሪ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱን የልማት ኣቅጣጫውንም በኣእሙሯቸው ኣመንጭተው በብእራቸው የነደፉ እጅግ ባለምጡቅ ኣእምሮም ነበሩ።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአገራችን ህገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ ፤ የሁሉም ህዝቦች እኩልነትና የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ህገ መንግሥታዊ ዋስትና አግኝተው በተግባር ላይ እንዲውሉ በአገራችን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና በድህነት የሚማስኑ ወገኖችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀ ተግባር የፈጸሙ ፤ ያደረጉ ኢትዮጵያን በአዲስና ጽኑ ዴሞክራሲያዊ መሰረት ላይ ያዋቀሩ ታላቅ መሪ ናቸው ።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አገራችንን በከፍተኛ ደረጃ ለመለወጥ የሚያስችለው የታላቁ የ5 ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሃንዲስ ከመሆናቸውም በላይ  ካደረባቸው ህመም ጋር እንኳ እየታገሉ የልማት ተግባራዊነቱን የመሩና አገራቸው የጀመረችውን ተከታታይና ፈጣን ዕድገት የማስመዝገብ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያደረጉ ታላቅ ቁርጠኛ መሪ ናቸው።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለኣፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ኢትዮጵያ ለኣፍሪካ ቀንድና ለኣፍሪካ ሠላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ፤ ኢትዮጵያ ፤ ለሶማሊያ ፤ ለደቡብና ሰሜን ሱዳን ፤ ለሩዋንዳ ፤ ለቡሩንዲ እና ለላይቤሪያ ዘላቂ ሠላም ታሪክና መላ ኣፍሪካውያን የማይዘነጉት አስተዋጽኦ እንድታበረክት ያደረጉ በኣህጉርና በዓለም ኣቀፍ ደረጃ ተፈሪና ተፅእኖ ፈጣሪ ታላቅ መሪ ናቸው።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የኣፍሪካ ሕዝቦች ድምጽ እንዲሰማ ኣፍሪካ በንግድና በልማት ፤ በዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ፤ በሠላምና መረጋጋት አቅጣጫ እንድትጓዝ ታላቁን የኔፓድ ፕሮግራም ከአፍሪካውያን የትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ያመነጩና ይህን ኣህጉራዊ ተቋም በኣገራቸው ውስጥ ተግባራዊ በማድረግ ኢትዮጵያ በእርግጥም የተለመደ አፍሪካዊ ኃላፊነቷን ከውስጧ በመጀመር እንድትወጣ ያበቁ ታላቅ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ህዳሴ መሪ ናቸው።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በዓለማችን ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ክፍፍል ሥርዓት እንዲዋቀር የታዳጊ አገሮች ድምፅ በመሆን በዓለም አደባባባይ የተሟገቱና ተቀባይነት ያተረፉ ታላቅ መሪ ነበሩ። በዓላማችን የተፈጥሮ ሀብት ሚዘን እንዲጠበቅ፣ በቃላቸው መሰረት ኢትዮጵያ የአረንጓዴው ልማት ሃሳባቸው ተግባራዊ ማሳያ እንድትሆን ያደረጉ ታላቅ ፤ በሳል ፤ በዓለም ኣቀፍ ደረጃ ተፈሪና ተፅእኖ ፈጣሪ መሪ ናቸው።

 

በብስለታቸውና በአርቆ አሳቢነታቸው በአገራችን ቦግ ብሎ የበራውን የተስፋ ሻማ የለኮሱ ኢትዮጵያንና መላውን የጥቁር ማህበረሰብ ያኮሩ ፤ መላው ዓለም ብቃታቸውን የመሰከረላቸው ታላቅ መሪ ናቸው።

 

እኤአ በ2003 ቶጎ/ሎሜ ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ መሪዎች ስበሰባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ አዲስ አበባ መሆኑ ቀርቶ የሊቢያዋ ትሪፖሊ እንድትሆን የአህጉሩን መሪዎች ማግባባት የጀመሩት የቀድሞው የሊቢያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ “አዲስ አበባ የምንሄደው ቆሻሻ ለማሽተት ነው? ስለዚህ ከቆሻሻዋ ከተማ ይልቅ ትሪፖሊ የህብረቱ መናገሻ ልትሆን ይገባል” ሲሉ ተናግረው ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በነዳጅ ዘይት ሀብት አቅላቸውን የሳቱትን ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊን ሲከራከሩ “እውነት ነው ከተማችን ቆሻሻ በዝቶባት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አገራችን ቆሻሻ ታሪክ የላትም” ሲሉ መመለሳቸውን ይዘከራል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና ትግራይ፦

=======================

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለትግራይ እና ተጋሩ ቢያንስ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ተመጣጣኝ እና ፍትሃዊ የመልካም ኣስተዳደር እና የልማት ተጠቃሚነት ኣስፍነዋል ወይ? የሚለው ትግራይን ያየ ይመስክር።

 

?

 

?

 

?

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የኣማራ ተወላጅ ቢሆኑ ኖሮ፦

===============================

በእርግጠኝነት “ታቦት ይቀረፅላቸው ኣይቀረፅላቸው” የሚል ክርክር ይነሳ ነበር።

 

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዕረፍት፦

=====================

(እኔ የግብፅና የCIA እጅ እንዳለበት ኣምናለሁኝ)

 

በ1997 ዓ/ም. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እስካሁን ግልጽ ያልሆነ የጤና ምርመራ በታላቋ ብሪታንያ ፤ ደቡብ ምዕራብ በሚገኝና ፓርክሳይድ በሚባል የግል ሆስፒታል አድርገው ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡

 

ሰኔ 2004 ዓ/ም በፊንፊኔ በተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ሰሚት ጉባዔ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን አለመገኘትን ተከትሎ  ጤናቸው መታወኩ ታወቀ፡፡ ተቃዋሚ ቡድኖች ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በቤልጅየም ህክምና ላይ ሳሉ ሰኔ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ህይወታቸው አልፏል ቢሉም፣ ተቀዳሚ ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግን የመለስ ህመም ለክፉ የማይሰጥ ነበር፡፡ ይሁንና ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ነሐሴ 14 ቀን ሰኞ ዕኩለ ሌሊት ላይ በተወለዱ በ57 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡

 

መለስ ከህግ ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሶስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ታሪክ በከፍተኛ የህዝብ ፍቅር ፤ በክብር እና በመዓረግ በዓለም መሪዎች ፊት የተቀበረ የመጀመሪያው መሪ ነው።

 

መለስ በንፁሃን እና ትክክለኛ ኣመለካከት ባላቸው የዓለም ህዝቦች ንፁህ ልብ እና የሱ ስም ሲነሳ በሚያቅለሸልሻቸው እንክፎች ጭንቅላት ዘንድ ለዘላለም በኩራት ይኖራል!

 

እግዚኣብሄር ድንቅ ፍጥረቱን መንግስተ ሰማያት ያውርስልን።

Comments

comments