መንግስት ጣት መቁረጥ ጀመረ

መንግስት በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን እና ነጋዴዎችን ዛሬ በቁጥጥር ስር ማዋል ጀመረ።

ሰፊ ጥናት እና ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቶ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

መንግስት እስካሁን ለህብረተሰቡ ቃል ሲገባ የነበረውና በተደጋጋሚ ሲገለፅ የነበረው የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት እርምጃ በከፍተኛ ደረጃ መጀመሩን የሚያመላክት ነው የተባለው ይህ ኦፕሬሽን በቀጣይ ቀናትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር የዋሉትን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና ነጋዴዎች ማንነት ዝርዝር እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

Comments

comments