150 አገራትን ተጎጂ ያደረገውን የሳይበር ጥቃት መንግስታት እልባት እንዲሰጡት ማይክሮሶፍት ጠየቀ

150 አገራትን ተጎጂ ያደረገውን የሳይበር ጥቃት መንግስታት ትኩረት ሰጥተው መፍትሄ እንዲሹለት ማይክሮሶፍት አስጠነቀቀ። ካለፈው አርብ ጀምሮ 150 አገራትን ያዳረሰው የሳይበር ጥቃት ኩባንያዎች የያዟቸውን መርጃዎች እስከመሰረዝ የሚያደርስ መሆኑን ነው ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ ያስታወቀው።

ከአሜሪካ የደህንነት ቢሮ ተሰርቆ የወጣ ነው በተባለው ሶፍት ዌር በመረጃ ቫይረስ መልክ ተለቆ ነው ጥቃቱ እየተፈፀመ ያለው።

ማይክሮሶፍት ዛሬ እንዳስታወቀው በተለይም የመረጃ ቋቶች በሶፍት ዌር ላይ እንዲጠለጠሉ ማድረጋቸው ለቫይረሱ አጋልጧቸዋል።

በመሆኑም ችግሩ ከዛሬ ጀምሮ አየሰፋ ሊሄድ ይችላል መባሉን ተከትሎ መንግስታት ይበልጥ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሚያሳይ የማንቂያ ደወል እንደሆነ ኩባንያው አመልክቷል፡፡አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልጉለትም ጥሪ አቅርቧል።

መንግስታት ያሉዋቸውን መረጃዎች ተጋላጭ በሆኑ ሶፍትዌሮች ላይ ማስቀመጣቸው በመረጃ በርባሪዎች እጅ እንዲገባ ስለሚያደርገው የመጠቀሚያ ኮምፒውተሮቻቸውን በፀረ ቫይረስ ሊያፀዱ እንደሚገባ መክሯል።

ራንሰምዌር “ransomware” የተሰኘው ቫይረስ ሰኞ እለት ተገልጋዮች ወደ ስራ ሲገቡ የሚጠቁ ኮንፒተሮች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ስጋት ቢኖርም እስካሁን የተጠቃው ቁጥር ግን በቁጥር አነስተኛ ነው ተብሏል፡፡

በርካታ ተቋማት የቫይረስ ጥቃቱን ለመከላከል ባለሞያወቻቸውን አሰማርተው የቆዩ ሲሆን ቫይረሱ ኮንፒተሮችን ካጠቃ በኋላ የ300 ዶላር ክፍያ እንደሚጠይቅ ተገልጿል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ ከ200 ሺህ በላይ ኮንፒተሮች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

Comments

comments