ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲችን በድጋሚ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ድራገን ፖፓዲችን በድጋሚ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ።

ኢትዮጵያ ቡና በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቡን የሚመሩትን አሰልጣኝ በትላንትናው እለት በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጹ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም ክለቡ የአሰልጣኙን ድራጋን ፖፓዲች ጋር በዛሬው እለት ተፈራርሟል።

በክለቡ የ41 ዓመት ታሪክ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር አሰልጣኝ ሆነው በ2008 ክለቡን የተቀላቀሉት ሰርቢያዊው ድራጋን ፖፓዲች ከአንድ አመት በኋላ ነው በድጋሚ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀሉት።

በ2008 የውድድር ዘመን ኢትዮጵያ ቡናን በሊጉ 2ኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ያስቻሉት ፖፓዲች፤ ውላቸው ባለመታደሱ ከክለቡ ተለያይተው የታንዛኒያው ክለብ የሆነው አፍሪካን ሊዮንስን ለአጭር ግዜ ካሰለጠኑ በኃላ ከስራ ርቀው ቆይተዋል።

ለሁለተኛ ጊዜ ክለቡን የተረከቡት ሰርቢያዊዉ አሰልጣኝ ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ክለቦች የማሰልጠን ልምድ ያለቸው ሲሆን፥ የጋናውን ኸርት ሶፎክ እና የታንዙኒያውን ቺምባ ክለቦች ማሰልጠናቸውም ታውቋል።

Comments

comments