ህንዳዊው ታዳጊ የአለማችንን ቀላል ሳተላይት ፈበረከ

ህንዳዊው ታዳጊ ሪፋት ሻሮክ የአለማችን ቀላልና በመጠን አነስተኛ የተባለለትን ሳተላይት መፈብረኩ ተነግሯል፡፡ሳተላይቱ 64 ግራም ክብደት ያለው ሲሆን የአሜሪካው ብሄራዊ የህዋ ሳይንስ ጥናት ኤጄንሲ ናሳ ባካሄደው ውድድር ላይ ታዳጊው ፈጠራውን አቅርቧል፡፡

ሳተላይቱ በመጪው ወር ውስጥ በናሳ ድጋፍ ሰጪነት ወደ ህዋ የሙከራ በረራ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ይህች ሳተላይት ቢያንስ ለ12 ደቂቃዎች ያህል አገልግሎት ትሰጣለች፡፡

የ18 አመቱ ታዳጊ ሪፋት ሻሮክ እንደገለጸው የፈጠራው አለማ በስሪዲ ቴክኖሎጂ የሚሰሩ ካርበን ፋይበሮች ምን ያህል ጠቃሚ መሆናቸውን ለማሳየት ነው፡፡

ይህቺ አነስተኛ ሳተላይት ከወዳደቁ እቃዎች እንደተሰራችና ስያሜዋንም በታዋቂው የህንድ መሪ በነበሩት አብዱል ካላም ስም ካላምሳት ተብላ መሰየሟ ተገልጿል፡፡

Comments

comments