የፈረንሳይ እጩ ፕሬዚዳንትና የባለቤታቸው የእድሜ ልዩነት በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል

በፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የአሸናፊነት ግምት የተሰጣቸው ማኑኤል ማርኮን እና በባለቤታቸው መካከል ያለው የእድሜ ልዩነት በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።

ሁለቱ ጥንዶች መካከል ያለው የእድሜ ልዩነት 24 ዓመት ሲሆን፥ በርካቶችም መነጋገሪያ አድርገውታል ነው የተባለው።

ወጣቱ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ይሆናል ተብለው ሰፊ ግምት የተሰጣቸው የ39 ዓመቱ ማኑኤል ማርኮን ባለቤታቸው የ64 ዓመት ሴት መሆናቸው ነው መነጋገሪያ የሆነው።

MARKON_3.jpg

ሁለቱ ጥንዶች የተገናኙት በትምህርት ቤት ሲሆን፥ በወቅቱም ማርኮን ተማሪ ባለቤታቸው ብሪጌት ደግሞ መምህር ነበሩ።

ታዲያ ማርኮን የ15 ዓመት ታዳጊ እያሉ መምህርቱ ብሪጌት ደግሞ የ42 ዓመት ጎልማሳ ሆነው ነበር የፍቅር ግንኙነት የጀመሩት።

MARKON_2.jpg

ማርኮን በወቅቱ ከመምህርቱ ፍቅር እንደያዛቸው እና ሊያገቧቸው እንደሚፈልግ ለወላጃቸው ቢናገርም ከወላጃቸው ዘንድ የጠበቀውን ምላሽ አላገኙም።

ወላጆቻቸውም የልጃቸውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውበት እንደነበረ ነው የተነገረው።

ሆኖም ግን ሁለቱ ጥንዶች ተግባብተው ማርኮን በወቅቱ የ3 እናት ልጆች የነበሩትን መምህርቱን ማግባታቸው ነው የተነገረው።

Comments

comments