የራበው ባል ለእራት የቀረበላቸውን ምግብ ፎቶ እያነሳች በማህበራዊ የትስስር ገፅ በማጋራቷ ሚስቱን ፈቷታል

የራበው ዮርዳኖሳዊው ባል ሚስቱ ለእራት የቀረበላቸውን ምግብ ፎቶ እያነሳች በስናፕቻት የማህበራዊ የትስስር ገፅ በማጋራቷ ፈቷታል፡፡

ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው፤ ቅዳሜ ዕለት ምሽት ባል እና ሚስት እራት ለመብላት አማን ውስጥ ወደ ሚገኝ አንድ ቅንጡ ሬስቶራንት ይሄዳሉ፡፡

ሬስቶራንቱም በጣም የተጨናነቀ ስለነበር ምግብ ሳያገኙ ለግማሽ ሰዓት ያህል ቆዩ፡፡

የምግብ መለያ ቁጥራቸው በይጠብቁን ሰሌዳ ውስጥ በመሆኑ ባል ድንገት ርሃብ ይሰማዋል፡፡

እንደዮርዳኖስ መገናኛ ብዙኃን መረጃ ምግቡ ደርሶላቸው ባል ሚስቱን እንብላ ሲላት ሚስት አይ ስልኬ ላይ ያፈጠጥኩበትን ስራ አልጨረስኩም ትላለች፡፡

በዚህ ሳታበቃ ምግቡን በስማርት ስልኳ ማንሳት እና ለጓኞቿ በማህበራዊ የትስስር ገፁ መላክ እና ማጋራትን ስራየ ብላ ተያያዘቸው፡፡

ባልም ይህ የሚስቱ ስራ ሲበዛበት ስለራበውም ጭምር እንድታቆም ይከለክላታል፡፡

ሚስት ግን ከስራዋ ባለማቆም የራበውን ባሏን ለብስጭት ትዳርገዋለች፡፡

ሁኔታው እየተባባሰ ሄዶ ባል ድንገት ድምጹን ከፍ አድርጎ በሀገሬው ቋንቋ “ጠላቅ” ወይም ፈትቼሻለሁ ብሎ፥ የምግቡን ሂሳብ ሳይከፍል ወጥቶ መሄዱን የዮርዳኖስ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

 

Comments

comments