የለንደን ማራቶንን እንደ ጎሬላ በመራመድ በስድስት ቀኑ የጨረሰው እንግሊዛዊ ፖሊስ

እንግሊዛዊው ፖሊስ በለንደን ማራቶን አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችሏል።

ቶም ሃሪሰን የተባለው የ41 አመት ፖሊስ በውድድሩ ልክ እንደ ጉሬላ በጉልበቱና በእጁ እየዳኸ ረጅሙን ርቀት ጨርሶታል።

በዚህም ሁለት እጁን እና ጉልበቱን በመጠቀም 42 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትሩን ጨርሷል።

ጉሬላው የሚል ስያሜ የተሰጠው ፖሊስ ሃሪሰን ረጅሙን ማራቶን በዚህ መልኩ ጀምሮም በስኬት አጠናቆታል።

ውድድሩን ለማጠናቀቅ ደግሞ ስድስት ቀናትን ፈጅቶበታል።

man_in_gorilla.jpeg

ፊቱን የጎሬላ ምስል ጭምብል በማጥለቅ ሲሸፍን፥ በእጁ እና እገሩ ላይም ግዙፉን የዱር እንስሳ የሚያስመስለውን አልባሳት ተጠቅሟል።

ፖሊስ ሃሪሰን በቀን ከ10 እስከ 12 ሰዓታትን በእጁ እና በጉልበቱ እየዳኸ አመሻሽ ላይ በወዳጆቹ ቤት አረፍ እያለ ነበር ውድድሩን የጨረሰው።

ሃሪሰን ይህን ሃሳብ ያመጣው ለጉሬላዎች የሚውል የእርዳታ ገንዘብ ለማሰባሰብ በማለም እንደሆነም ተናግሯል።

በዚህ ሀሳቡም በሩጫው ብቻ 42 ሺህ 700 የአሜሪካ ዶላር ማሰባሰቡም ነው የተነገረው።

change.jpeg

ገንዘቡ በምስራቅ አፍሪካዎቹ ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ ለሚገኙ ጎሬላዎች መንከባከቢያ ይውላል ተብሏል።

በመጨረሻም እሁድ የጀመረውን ማራቶን ቅዳሜ በመጨረስ ሃሳቡን አሳክቷል።

የሩጫው ማጠናቀቂያ መስመር ላይም ሁለቱ ልጆቹ ሲቀበሉት፥ ግዙፉ የዝንጀሮ ዝርያ እንደሚያደርገው በአሸናፊነት መንፈስ ደረቱን እየመታ ውድድሩን ማጠናቀቁን አውጇል።

Comments

comments