አባጨጓሬ ላስቲክ እንዲመገብ በማድረግ ቆሻሻ መከላከል እንደሚቻል ሳይንትስቶች ገለጹ

የካምብሪጂ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች  ከንብ ቀፎ ውስጥ ሰም የሚበላው  የአባጨጓሬ እጭ ላስቲክ  በመብላት የላስቲክ ብክለትን ሊቀንስ እንደሚችል ይፋ አድርገዋል፡፡

ሳይንትስቶች በዘርፋ ያደረጉት ምርምር እንደሚያመለክተው ነፍሳቶቹ በላስቲክ የተጠቀለሉ ኬሚካሎችን እንደ ሰም መሰባበር ይችላሉ፡፡

በየአመቱ በዓለም ዙሪያ 80 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የላስቲክ ጥቅሎች ይመረታሉ፡፡

እነዚህ ላስቲኮች ለእቃ መያዣነት፣ ለምግብ መጠቅለያነትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ  ሲሆን ከአገልግሎት በኋላ የሚጣሉት ላስቲኮች ግን  ወደ አፈርነት ለመቀየር ብዙ አመትት  ይፈጅባቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሳይንቲስቶቹ ባገኙት ጥነት መሰረት የአባጨጓሬ እጮች የላስቲክ ጥቆሎችን  በሰአታት ጊዜ ውስጥ የመበጣጠስ አቅም አላቸው፡፡

ሳይንትስቶቹ በቀጣይ የላስቲክ ቆሻሻች ችግሮች በዚህ ዘዴ የመቅረፍ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል ቢቢሲ እንደዘገበው፡፡

Comments

comments